በቤተ ክርስቲያናችን ካሉ ከ፲፬ቱ ፍሬ ቅዳሴያት በተጨማሪ የተወሰኑ የጒባኤ ሊቃውንት ብቻ የሚያውቋቸው ለምእመናን ዐይን ያልበቁ ሌሎች ፍሬ ቅዳሴያት አሉን፤ ለምሳሌ ያኽል አራት የቅዳሴ ማርያም ፍሬ ቅዳሴያት በብራና በግእዝ ተጽፈው ሲገኙ፡- እነዚኽም
፩ኛ) ቅዳሴ ማርያም ዘናትናኤል ሐዋርያ የሚል (መጽሐፉ በጎጃም ደብረ ማርቆስ የነበረ)፡፡
፪ኛ) ቅዳሴ ማርያም ዘማርቆስ ወንጌላዊ የሚል (መጽሐፉ በዜና ማርቆስ ገዳም የነበረ)፡፡
፫ኛ) ቅዳሴ ማርያም ዘጎርጎርዮስ ዘቀጶዶቅያ (መጽሐፉ በጣና በጣሬጣ የነበረ)፡፡
፬ኛ) ቅዳሴ ማርያም (መዐዛ ቅዳሴ) በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተደረሰው ነው፡፡