MENU

Fun & Interesting

“የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል።”  መዝሙር 34፥19. በመልአከ መንክራት ቀሲስ ጌታቸው

Video Not Working? Fix It Now

ጥር 18 የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አጽሙ …ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉስሥ ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እሳት እንዲያነዱበት አደረገ የሰማእቱን ሰጋ አቃጠሉት ፈጩት አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው ወታደሮቹ የታዘዙትን ፈጽመው ተመለሱ። ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሰረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በብሩሕ ደመና ወረደ በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማእቱን ስጋ እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ፤ ከዚህ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው ህልቶን፤አግሎሲስ፤ሶሪስና አስፎሪስ ነው፤ ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፤ በኃላም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። ይህ የሆነው ጥር 18 ቀን ነው ይህንንም ቀን " ዝርዎተ አጽሙ " ስትል ቤተክርስቲያን ሰማእዕቱን አዘክራ ትውላለች። ሁላችንንም በያለንበት የሰማዕቱ በረከት ተሳታፊ ያድርገን። አሜን

Comment