ቆየት ካሉት ወደ ንስሐ ከሚመሩ መዝሙራት አንዱ! የቀሲስ አበበ ተሰማ መዝሙራት ከሆኑት. `ተመከር ሰው ሆይ,
ተመከር ሰው ሆይ
ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር(፪)
መላ ሰውነትህን አስገዛ ለእግዚአብሔር
ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)
እጅና እግርህ ታስሮ ሳትወርድ ወደ መቃብር
ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)
ተሰብከዋል እና በዓለም ቅዱሳት መጻህፍት ለአንተ ለመመስከር
ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)
የእግዚአብሔር ሕጉን በአንዱ ጆሮ ሰምተህ በአንዱ ማፍሰስ ይቅር
ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር(፪)
ቀሲስ አበበ ተሰማ