By Mehret Debebe, Consultant Psychiatrist and Trainer - ይህ ፖድካስት ጠቃሚና ለህይወት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ዶክተር ምህረት ከሌሎች በሚነሱት ጉዳዮች ላይ ዕውቀትና ጥበብ ካላቸው አንጋፋ ባለሙያዎች ጋር ያሚያደርገው ውይይት ነው።
ዶ/ር ወንድወሰን የነርቭ ሕክምና ስፔሻሊስትና የስትሮክ ሳብ-ስፔሻሊስት (Interventional Neurologist) ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ ከ90% በላይ ጊዜያቸውን ሰጥተው በኢትዮጵያ ውስጥ ከባለቤታቸው ሲስተር ፋሲካና አጋሮቻቸው ጋር በከፈቱት አክሶን የስትሮክና የስፓይን ማዕከል ውስጥ በማከም፣ በማስተማርና በመራመር ስራ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ። በቀረው ጊዜያቸው ደግሞ በአሜሪካን ሀገር በቴክሳስ ዩኒቨስቲ ውስጥ በተባባሪ ፕሮፌሰርነትና በሀኪምነት ተመሳሳይ ሥራን ይሠራሉ። ጊዜያቸውን ሰጥተው ስላካፈሉን ዕውቀት እናመሰግናለን። ሙሉ ሥራቸውንና ታሪካቸውን በዝግጅቱ ውስጥ ትከታተሉ ዘንድ ጋብዘናችኋል።