በ "ሐዋዝ ሀሳብ" ዩቲዩብ ቻነላችን በሰናይ ሰብዕናቸው ፤ በመልካም ተምሳሌትነታቸው ፤ እንዲሁም በተፅኖ ፈጣሪነታቸው ፤ ታዋቂነትን ብቻ ሳይሆን አዋቂነትንም የተጎናፀፉ ቅን ግለሰቦችን እናቀርባለን፡፡ ሸጋና ቀና ሀሳብ ያለው ጥበበኛ ሁሉ ቤተኛችን ይሆናል፡፡ ጥሩዎች በበጎነት ዙሪያ ትርጉም ያላቸው ስራዎቻቸውን በደግነት ያጋራሉ፡፡ ሀገርና ትውልድ የሚገነባበትን ፍሬ ብስል የጥበብ ሥራቸውንም ያቀርቡበታል፡፡ በሀሳብ ድንበር ሳንከለል ነፃ በሆነ አስተሳሰብ ነፃ የሆነች ጥበብን እናጋራለን፡፡