ፋና_ወጊ የለውጥ አቀንቃኝ መሪዎች በኢትዮጵያ_#HistoricalEthiopianLeaders #Historical#EthiopianLeaders #ethiopian Intellectual@rvleaders
ለኢትዮጵያ ነጻነትና ጽናት ወሰንዋን ጠብቆ አሳፍሮ አስከብሮ ለማኩራትና የሕዝቧ ልብ የታመነ ኃይል እንዲኖረው ለማድረግ መሣሪያው ትምሀርት መማር ነው። […] በዚች ተማሪ ቤት ያቆምሁት የውጭ ቋንቋና ጥበብ ብቻ አይደለም፣ የሀገራችንም ቅዱሳት መጻሕፍት ወልድ ዋህድ ሃይማኖት የሚነገርበት ናት። የሀገሩንም ትምህርት ጽሕፈት ቋንቋ እንድሚገባው የማያውቅ የውጭውን እማራልሁ የሚል ምሳሌው ቀዛፊ እንደሌለው ታንኳ ነው።
Education is essential to safeguard Ethiopia’s independence, to ensure that its borders are respected and made inviolable, to make it proud and to make the people aware of its strength. […] It is not only to teach foreign languages and sciences that I founded this school but also to teach the holy books of our country and faith in the only son of God. Anyone who wants to learn foreign education before learning enough of the literature and language of his country is like a boat without oars.5
#ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ
ደራሲው ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ሲሆኑ የልብወለድ ድረሰታቸው 'ጦቢያ' ትባላለች። አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በ1860 ዓ. ም ዘጌ(#ጣና #ሀይቅ) በተሰኘችው ስፍራ ተወለዱ፡፡ የ#እቴጌጣይቱ ብጡል የሥጋ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው አፈወርቅ በልጅነት ዕድሜያቸው አዲስ አበባ መጥተው አደጉ። ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ያውሮፓን ሥልጣኔ ቀስመው እንዲመጡ ወደውጭ ሀገር ከላኳቸው ብልህ ወጣቶች መካከል አንዱ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ናቸው። አፈወርቅ ባማርኛ ከጻፍዋቸው መጻሕፍት፣የአጤ ምኒልክ ታሪክ” እና “ልብ ወለድ ታሪክ”ጦቢያ'
#ኦነሲሞስ ነሲብ (1856-21,ሰኔ,1931)
ኦነሲሞስ ነሲብ የሉተራንን እምነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወስዶ መጽሀፍ ቅዱስን ወደ #AFAN OROMO የተረጎመ የ#ወንጌል ሰው ነዉ፡፡
ኦነሲሞስ ነሲብ በልጅነቱ ባሪያዎችን በሚሸጡ ሰዎች በ 1869 ታፍኖ እንደ ባሪያ ተሸጠ ነበር፡፡ ባጠቃላይ
ነሲብ ከ 4 ጊዜ በላይ በተለያየ ሰዎች ተሸጦ ያውቃል፡፡
በኋላም ዋርነር ማዚንገር(1832-1875) የሚባል የፈረንሳይ ምክትል ቃልአቀባይ የሆነ ሰው በምፅዋ #ኤሪትሪያ ነፃ አወጣዉ፡፡
በመቀጠልም በስዊድን የወንጌል ሚሽነሪ(Swedish evangelical mission) እነሱ ጋር መጽሀፍ ቅዱስን ለመማር እድልን አገኘ፡፡ ኢሙኩሉ በሚባል ቦታ ወንጌልን ተማረ፡፡ ኦነሲሞስ ከልጅነቱ ጀምሮ በኦሮሞ ማህበረሰብ ቢያድግም ቋንቋዎችን በደንብ ስለማያውቅ እርዳታ አስፈለገዉ ስለዚህ እሱን ልትረዳ ምትችል #አስቴርገኖ(1874-1964)አገኘ፡፡
አስቴር ገኖ እና ኦነሲሞስ ነሲብ አብረዉ #መጽሀፍ ቅዱስን ወደ #afanoromo ለመጀመሪያ ጊዜ ተረጎሙት።
ሚሊዮኖች የእግዚአብሔርን ቃል በቋንቋቸው እንዲያነቡ ያስቻለው ኦነሲሞስ ነሲብ በተወለደ በ 75 አመቱ እሁድ ሰኔ 21 1931 ከዚህ አለም በሞት ።
ኦነሲሞስ ነሲብ ታላቅ እና የማይረሳ ታላቅ ሰዉ ።
የወንጌል #አርበኛ ኦነሲሞስ ነሲብ።
#ሐኪም #ወርቅነህእሸቴ የኢትዮጵያ ምርጥ ልጅ ነበሩ።
አዛዥ ወርቅነህ / ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ የመቅደላ ጦርነት ጊዜ በእንግሊዝ የጦር መኮንን በሕጻንነታቸው ወደ ሕንድ አገር ተወስደው እዚያው ያደጉ፤ የኖሩ እና በቀዶ ጥገና ሙያ የተሠማሩ ሰው ሲሆኑ አሳዳጊ አባቶቻቸው በሰጧቸው ስሞች ቻርልስ (በወሰዳቸው መኮንን ስም)፤ ማርቲን (ባሳዳጊያቸው ሐኪም ስም) (Charles Martin) ይባሉ ነበር። #አዛዥ ወርቅነህ በሎንዶን የኢትዮጵያ ዋና መላክተኛነቱን ሥልጣን ሲሾሙ የሹመት ማስረጃቸውን መጀመሪያ ለንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም፤ በኋላ ደግሞ ለንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም አቅርበዋል። በዚህ ዕለት የኢትዮጵያን ግዛት ከግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ጀምሮ የምወክለው እኔ ነኝ ያለችው #የኢጣሊያ መላክተኛም የሹመት ማስረጃውን አብሮ አቅርቧል። በሎንዶን ፲፯ ‘#ፕሪንስስ ጌት’ (17 Princes Gate) የሚገኘውን የኢትዮጵያ መላከተኞች መኖሪያ እና መሥሪያ ቤትን በአገራቸው ስም የገዙትም ዋና መላክተኛ አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ናቸው።
#ገብረህይወት #ባይከዳኝ
ገብረ ህይወት ባይከዳኝ ትግራይ ጠ/ግዛት #አደዋ አውራጃ ዘንጎይ መንደር ከእናቱ ከወ/ሮ ህልፋ ወ/ስላሴ እና ከአባቱ ከሻቃ ባይከዳኝ ሰኔ 24 ቀን 1879 ዓ.ም ተወለደ፡፡ #የአጼ #ዮሐንስ ወታደር የነበሩት ሻቃ ባይከዳኝ ገና የ4 ዓመት ህፃን ሳለ ነበር በመተማ #ጦርነት ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው በኦስትሪያ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርቱን የተከታተለው ደግሞ በጀርመን አገር ነው፤ ከበርሊን ዩኒቨርሲቲ በህክምና ዶክተርነት ዲግሪውን የተቀበለው ገብረ ህይወት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሀኪም ከሆኑት ከ #ዶ/ር #ወርቅነህ (ሀኪም ወርቅነህ) ቀጥሎ የተገኘ ኢትዮጵያዊ ሀኪም ነው፡፡ በብዙ መልኩ ከዘመኑ የቀደመ፣ በጥልቅ አሳቢነቱና ዘርፈ ብዙ ዕውቀቱ የተደነቀ፣ በአነጋገሩ ደፋር፣ ለህዝብና ለአገር ለውጥ ብዙ ራዕይ የነበረው ሰው ነው ገብረህይወት። እርሱን በቅርብ ከሚያውቁት መካከል አንዱ ራስ እምሩ ሀይለ ስላሴ “ካየሁት ከማስታውሰው” በተሰኘው ተወዳጅ መጽሀፋቸው እንዲህ ጽፈዋል፦ ".....#ነጋድራስ ገብረ ህይወት የተማረ፣ በጣም ያስተዋለ፣መልካም ብርቱ ሰው ነበረ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ እንደእርሱ ያለ አስር የሚሞላ ሰው አልነበራትም::
#addisababa #univercity