አስደንጋጭ ነው አለልኝን ሚስቱ እንደገደለችው ማረጋገጡን ፍርድ ቤቱ አስታወቀ፡፡(@gizemedia1974) #Ethiopia| #elias |18 Jan 2025
አለልኝ አዘነ እራሱን አላጠፋም ፣ ፍርድ ቤት ክስ ላይ
የሰው ልጅ ኖኩ ትላንትን ተሻግሬ ነገን አየሁ ብሎ ባለ ቁጥር አንድ እርምጃ ወደ ሞቱ እየቀረበ እንደሆ እሙን ነው፡፡ ይህንን እውነት ግን ማንም ሰው ማመን አይሻም…ሁሉ ሰው ሁሉ ፍጡር እንደ ጓያ አረም የፊት የፊቱን ብቻ እያስተዋለ ወዲያ ማዶ አሻግሮ ሞት ይሉት ነገር እንዳለ አንድ ቀን …ከምንወዳቸውም ከሚወዱንም ሰዎች እንደሚለየን ማሰብ አንሻም! ከሞት አማሟት ይከፋል…. ከሞትም በላይ አሟሟት በቁም ያለን ሰው ይበላላ …ለወላጅ ልጄን ብሎ ማልቀስ በራሱ ከሞቱ ይከፋል! ደግሞ ወዲህ ይስመር ይመርልኝ …ብለው የፍቅርን እንጎቻ እያበሰሉ …የመውደድንም ወጥ እየወጠወጡ …አብሮ ለመክረም …ሶስት ጉልጃ ለመጣድ በትዳር ለተጣመሩት የተጣመሩት ሰው ከጀርባ ሆኖ የሞት ድግስ እየደገሰ እንዲህ አጋሬ ያሉትን ለሀገርም ለቤተሰብም አለኝታ መከታ የሆነን ሰው ሕይወት መንጠቅ ልብ ውስጥ የሚፈጥረው ሕመም እና ስንጥቃት እንዲህ ነው የሚባል አይደለም፡፡
የቀድሞ የባህርዳር ተጫዋች የነበረው የአርባምንጩ ልጅ ፣ከብር 640 ሺህ በላይ ይከፈለው የነበረው እግር ኳሶ ተጨዋች አለልኝ አዘነ ራሱን አላጠፋም ፣
ከወራት በፊት ሙሉ የኳስ ተመልካችን ልብ የሰበረው ጉዳይ የቀድሞ የባህርዳር ተጫዋች የነበረው የአርባምንጩ ልጅ አለልኝ አዘነ አሟሟቱ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ላይ በዋለው ችሎት ክሱ ለማመን የሚከብድ ሆኖ ነበር የተሰማው ፡፡
ከብር 640 ሺህ በላይ ይከፈለው የነበረው ይህ አመለ ሸጋው እግር ኳሶ ተጨዋች አለልኝ አዘነ ራሱን አጠፋ የሚል ወሬ በሞተበት ወቅት ይሰማ የነበረ ሲሆን እንደ ዋነኛ ምክንያት የተሰማው ነገር ደግሞ ከቤተሰቦች ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ነው፡፡ ይህ አለመግባባት ነው ደግሞ በሚስቱ እና በቤተሰቡ ምክንያት እንደተፈጠረ ሲነገር ቆይቷል፡፡
ቤተሰቦቹ በቅርቡ በፈፀመው ጋብቻ ደስተኛ ባለመሆናቸው ጭቅጭቁ በርክቶ ነበር። ከገንዘብ አምጣ አላመጣም ጋርም እንደዚሁ ችግሮች እንደነበሩ ሲነገር ቆይቷል። ምናልባት ትዳር መመስረቱን ተከትሎ ፊቱን ወደዛ በማዞሩም የመጣ ሊሆን ይችላል የሚሉ መላ ምቶችም ነበሩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ለቤተሰቦቹ እያሰራ ከሚገኘው ቤት ጋር ተያይዞም የቤቱን ጉዳይ እንድታስጨርስ ኃላፊት የተሰጣት ታላቅ እህቱ እርሷ ጋር እንዲቀመጥ ያስቀመጠውን ብር በመከልከሏ ምክንያት ነው በሚል በተሰማው ወሬ ሳቢያም ቤተሰቦቹ ተይዘው ለቀናት ታስረውም ቆይተው ነበር፡፡ ኃላ ላይ አሁን ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር የዋሉት ሚስቱ እና ተባባሪዎቿ ከተያዙ በኃላ እንደተሰማው ከሆነ ይህን ወሬ ይሁነኝ ብላ ያስወራችው እና ለሞቱ ተጠያቂ እንዳትሆን ጉዳዩን ከራሷ ለማሸሸ እንዳስወራቸውም ታውቋል፡፡
ይሁንና ህግ ጉዳዩን ይዞ ስያጣራና ስመረምር ቆይቶ ከዋራት በፊት በዋለው ችሎት የተሰማው ነገር በጣም ልብ ሰባሪ እና እንዴት ሆኖ ይህ ሊሆን ይችላል ያስባለ ጉዳይ ነበር ።በወቅቱ በዋለው ችሎት ላይ የክስ አቤቱታው የተነበበ ሲሆን በአቤቱታው ውስት በማስረጃ ተገልጠዋል ተብለው የተነሱ ነጥቦች እንደሚያስረዱት ከሆነ አለልኝ በገዛ ሚስቱና በእህቱ ባል በሆነ ግለሰብ አማካኝነት እራሳቸው በገዛ መኖርያ ቤቱ ውስጥ እንደገደሉት እና ገድለውተም ሲያበቁ እራሱን አለጠፋ ለማለት የመብራት እንጨት ላይ በገመድ አንጠልጥለውታል ፣ የሚል ነበር፡፡
ይህ ጉዳይ ሲሰማ ያልደነገጠ ሰው አልነበረም፡፡ እንደምን ደፈሩ በተለይ ሚሰትየው በምን ልቧ ጨክና እንዲህ አደረገችው እንዴት እንዴት ሆኖ ነው ይህ የሚሆነው የሚለው ጥያቄ ብዙ ብዙ ጭንቅላት አዙር ጥያቄዎችን ሲፈጥር ቆይቷል፡፡
እንኳን እና ከሌላ ሰው ጋር አብራ ተባብራ ነፍሱን ልትነጥቀው ቀርቶ …በቤተ ክርስቲያን ሕግ ሲጋቡ ቢያጣ ቢነጣ ታመመ …የአልጋ ቁራኛ ሆነ ብላ ላትከዳው ከርሱም ሌላ ሰው ላታይ በመኃላ አግብታው እንደምን እንዲህ ልታደርገው ቻለች የሚሉ ጥያቄዎች ዛሬም ድረስ አልተፈቱም፡፡
ሚስት አደይ ጌታቸው አለልኝ ከሞተም በኃላ ሳታርግዝ ለባህርዳር ከነማ ተጫዋች ጔደኞቹ ልጁን በሆዴ ይዣለሁ ነፍሰ ጥር ነኝ በማለት እንደዋሸቻቸው እና ተጫዋቾቹም ሆኑ ክለቡ እንዲረዳት አስደርጋ 417 ሺ ብርም እንተቀበለች አውቀናል ሲሉም የአልኝ ቤተሰቦ ገልፀዋል፡፡እንደ አለልኝ ወንድም ገለፃ ከሆነ አልኝ ከሞተም ወዲህ የተቀበረበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቤተሰቦቿም ሆኑ እርሷ እራሷ አንድም ቀን ሄደው መቃብሩ ላይ ሻማ አብርተውም ሆነ ሀውልቱን ውኃ አጠጥተው እንደማያዉቁ በከፍተኛ ሀዘን ይገልፃሉ፡፡፡
ወዲህ ደግሞ እርሷ በጭራሽ እንዲህ አታደርግም …ነገሩ በቲፎዞ እና በድጋፍ መታየት የለበትም መዳኘት ካለባትም በተጨበጠ መረጃ እና ማስረጃ ነው የሚሉ ሀሳቦችን የሚያነሱ ግለሰቦች አልጠፉም፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን ከዚህ ቀደም ከነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በኃላ ይንን ጉዳይ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ምን አይነት ውሳኔ ይሰጣል በክስ አቤቱታው ላይ እንደተባለው ሚስት እና ተባባሪ ተብለው የተከሰሱት ግለሰቦች ጥፋተና ሆነው ይገኛሉ ወይንስ ነፃ ይወጣሉ የሚል ጉዳዩን የማወቅ ጉጉት ነበር፡፡
ከዚህ በኃላ ሰሞኑን በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአለለኝ_አዘነ የሞት ጉዳይን በተመለከተ ችሎቱ ሚስቱናን እና የሚስቱ እህት ባል ጥፋተኛ ናችሁ ብሎ ብይን መስጠቱ ተሰምቷል፡፡(@gizemedia1974 )