MENU

Fun & Interesting

ትዝታ የመልሷ ቀን ለጔደኞቿ ያደረችውን ንግግር| (@gizemedia1974)#Ethiopia |#Eliasdegenet|28 Febr2025

Gize Media 10,685 5 hours ago
Video Not Working? Fix It Now

የትዝታ ነገር ዛሬም አንጀት አንጀታችንን እየበላን ..ሆድ ሆዳችንን እየቆጠን ይገኛል! መቼም ሁሉም ሰው ከሞት የማይቀር ፍጡር ቢሆንም ቅሉ …የአንዳንዱ ሰው አሟሟት እና የአሟሟቱ ነገር የዘላለም ፍም እሳት ከሆድ ውስጥ ትቶ ያልፋል፡፡ ትዝታ አሁን ምድር ላይ የለችም በሰማያዊው ቤቷ ግን ሕያው ሆና አለች!! በቀኝ ዘመኗን ሙሉ በናፈቀችው …ባከበረችው አባቷ እቅፍ ውስት ነች!! ቋሚ ተጎዳ እርሷስ ከእውነት ቦታ ነች እንዲሉ እርሷ ፍርዱም ከማይጓደልበት ርትሁ ከማንዛነፍበት ስፍራ ሄዳለች ምንም አትሆን ! በምድር ያሉ ወንድሞቿ ወዳጅ ዘመዶቿ …ጔደኞቿን ግን የሀዘን ዝገት ልባቸውን ይበላው ይዟል! ዳርናት ወልዳ ከብዳ ልናያት ነው ያሉ ሁሉ ህላማቸው …ፍላጎታቸው ሁሉ ፀሐይ እንደነካው ቅቤ ቀልጧል!! እርሳም ብትሆን ያሰከበች ያለመችው ሁሉ እንደተጨበጠ ጉም ሆኖባታል! እንድትወልድ እንድትከብድ ኩለው የዳሯት ወዳጆቿ ሁሉ ያቺን ጠንበለል ሰው በከፈን ከፍነው በሳጥን ቆልፈው ወደ ሀገሯ ሲሸኟት ልባቸው ነገሩን የእውነት እንደሆነ አምኖ ለመቀበል እየተቸገሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ትዝታ እንዲያ ባለ ሁኔታ ወደ ትውልድ ሀገሯ ወደ አዶላ ጉጂ ስትመጣም …ወፈ ሰማዩ ሁሉ ..ትልቅ ትንሹ የሚያውቃትም የማያውቃትም ሁሉ ነበር እያለቀሰ ..ደረት እየዳቃ የተቀበላት ፡፡ እንዲህ ያለችን ሰው ማጣት ሕመሙ ከቤተሰብ አልፎ እንዲህ ለማህብረሰብም ይተርፋል!! ወዲህ እንዴት …ለምን …በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም አናቷን ፈልጦ …አንገቷን ቀልቶ ተሰውሯል የተባለው ባል ደግሞ ከሕግ ተሸሽጎ ይገኛል …ባል አድነው አበበ ዛሬ ከሚገልጉት ሰዎች እና የሕግ አካላት ተደብቆ ተሸሽጎ ቢሰወርም ቀን ከሌት ከማይለየው ሕሊናው ግን መሸሽም መሸሸግም አይችልም! ይህ የማይካድ ሀቅ ነው… ደግሞ ልቡ ደንድንኖ …ባደረገው ነገር ፀፀት ይሉት ነገር ባይነካከው …በፍርድ ቀን የማይቀርለት ሰማያዊ ፍርዱን ስለማግኘቱ ግን ምንም አይነት ትርጠረት የለንም፡፡ ገድሎ ጥፍቷል ተብሎ ከተጠረጠረው ባል ጋርም ተያይዞ ከወዳጆቿ አካባቢ ተሰማ የተባለውም ነገር እጅጉን አስገራሚም አስደናቂም ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ ያለ ወንጀል ሰርቶ ተሰውሯል የተባለን ግለሰብ ለመደበቅ የሚሞክሩ ወዳጅ ዘመዶቹ አሉ …በአንዳንድ ቲክ ቶክም ላይ ብቅ እያሉ ነገርየውንም እርሱ እንዳለደረገው ማስተባበያ ለመስጠት እየሞከሩ መሆኑ መሰማቱ ደግሞ በተፈጠረው ቁስል ላይ ሌላ እንጭት የመስደድ ያህል ነው!!እንዲህ ካለ የጭካኔ ተግባር ጋር ሕብረት ለመፍጠር የሚሞከር ወዳጅነት በምንም መልኩ ቢለካ ቅዱስ አይደለም …ወዳጅነት …መተጋገዝ ..መተባበር በራሱ ቅዱስ የሆነ ሀሳብ ቢሆንም ቅሉ እንዲህ ባሉ ነገሮች ላይ ግን ባመበር እና መተባበር ከኩነኔው ፅዋ መቋደስ ነው፡፡ ያም አለ ይህ ግን የትዝታ እውነት እና ሀቅ እንዲሁ ቀርቶ አይቀርም…ያ ያመነችው ….በብዙ ያገለገለችው አምላኳም ደሟን በከንቱ አያስቀረውም፡፡ ዛሬ የትዝታን ነገር ደግመን ለማንሳት ምንንያት የሆነን በውስጥ መስመር የተላከልን አንድ ቪዲዮ ነው …ቪዲዮውን የቅርብ ወዳጆቿ የቀረፁት እና ለማህበራዊ ወደ ማህበራዊው ሚዲያ ላይ ያወጡት የሰርጓ ሰሞን የመልሷ እለት የተናገረችው …ወዳጅ ጓደኞቿን ያመሰገነችበት ምስል እና ድምፅ ነው … እዚህ ቪዲዮ ላይ ያሉ ሁሉ …በተለይ እንዲያ ወጓቧን በታመመችበት ወቅት ውለታ የሰሩላት እኛ እናት ሕመማቸው እንዴት እንደሆ አለማሰብ ነው የሚሻለው፡፡(@gizemedia1974 )

Comment