MENU

Fun & Interesting

የሀርላ ታሪክ/History of Harla ቀደምት ሀረሪዎች

Tarik History 9,910 3 months ago
Video Not Working? Fix It Now

የሀርላ ማኅበረሰብ ታሪክ ሀርላዎች በአሁኖቹ ኢትዮጵያ፣ ሶማልያ እና ጅቡቲ በሚኖሩ ነዋሪዎች ዘንድ የተለያዩ ታሪካዊ ግንባታዎችን እንደገነቡ ይነገርላቸዋል። ምንም እንኳ በአሁኑ ጊዜ የእነዚህ ግንባታዎች ፍርስራሽ ብቻ ቢገኝም እነዚህ ግንባታዎች የመቃብር ላይ ሐውልቶችን፣ የጉድጓድ ጎተራዎችን፣ መስጂዶችን እና ቤቶችን ያካትቱ ነበር። የዋሻ ላይ ስዕሎችን ራሱ ሀርላዎች እንደሰሩት ይነገርላቸዋል። በቃል በተላለፈ ታሪክ መሰረት ከሀርላ ዋና ከተማዎች አንዱ መተሀራ ነበር፤ እናም ከሀረር እና ከድሬዳዋ መካከል ያለው ቦታ አሁንም ሀርላ ይባላል። ሀርላዎች በአፍሪካ ቀንድ በጨርጨር እና በተለያዩ ቦታዎች በመስፈር ብዙ የመቃብር ላይ ክምሮችን አቁመዋል። የታሪክ አጥኚው ሪቻርድ ዋይልዲንግ እንዳለው ከሆነ ትረካዎች እንደሚያመለክቱት ሶማሌዎች እና ኦሮሞዎች ወደ አካባቢዎቹ ከመምጣታቸው በፊት ሀርላዎች በኦጋዴን ውስጥ አሸዋማ አካባቢዎች ላይ ኖረዋል። የሀርላ ግዛት ከ6ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ ግዛት ቢሆንም እስልምና በግዛቱ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር የጀመረው በ8ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነበር። በ9ነኛው መቶ ክፍለ ዘመንም በአፍሪካ ቀንድ የመጀመርያው የሙስሊም ግዛት የሆነው የማቅዙሚ ሥርወ መንግስት በሀርላ ሀገር ውስጥ ተነሳ። የማቅዙሚ ዋና ከተማ የሆነው ወላሌም የሚገኘው በሰሜን ሀረርጌ ነበር። የሀርላ ግዛት መሪዎችም ገራድ ተብለው ይጠሩ ነበር፤ የሐይማኖት ልሂቃን ደግሞ ካቢር የተባለ የክብር ማዕረግ ነበራቸው። በአካባቢው እንደሚነገረው አተራረክ ከሆነ ሀርላዎች አራወሎ የተባለች ንግሥት ነበረቻቸው። እርሷም የአፍሪካን ቀንድ አብዛኛውን ምስራቃዊ ክፍሎች ትገዛ ነበር። በዘይላም ሀርላ የተባለው ጎሳ ከጥንታዊው ህዝብ ጋር እንደሚተሳሰር ይናገራል። የዘይላ ነዋሪዎችም አሙድ የተባለው ጥንታዊ ከተማ በሀርላዎች እንደተገነባ ይናገራሉ። እንደ አባድር ኡመር አል-ሪዳ ያሉ የአረብ ስደተኛዎችም ወደ ሀርላ ግዛት በብዛት መግባታቸው 'ጌ' ተብላ የምትታወቀው የሀረር ከተማ እንድትመሰረት አድርጓል። ሀረርም በአፍሪካ ቀንድ ቀዳሚ የእስልምና ማዕከል ሆነች። የሥነ ቅርስ አጥኚው ቲመቲ ኢንሶልም በሀርላ ከተማ ውስጥ በሀረር ከተገኘው የሸክላ ሥራ ጋር የሚመሳሰል የሸክላ ሥራ አግኝቷል። ያህያ ነስረላህ በፃፈው ፋትህ መዲናት ሀረር በተባለው አረብኛ የሀረሪ ዜና መዋዕል መሰረት አባድር እንደ ኢማም በጸሎት መራና ስለ ግዛቲቱ አስጨናቂ ሁኔታ መረመረ። "ከጸሎት በኋላ መስጂድ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰዎች (ከመካ ከመጡት) በስተቀር ማንም አልቀረም። እርስ በርሳቸውም ‹ስለ እኛስ ምን አለን? አሚራቸውንም ሆነ ዊዚራቸውን አላየንም። ይልቁንም ሁሉም አንድ ደረጃ ያላቸው ናቸው። ከዚያም አንድ ሰው እንዲህ አለ፡- ‹‹ከ25 ዓመታት በፊትም ሞት እስኪያጠፋቸውና ከበሽታና ከረሃብ ሸሽተው እስከተበተኑ ድረስ ከ25 ዓመታት በፊት ሐርላ ሕዝቦች እንደነበሩ ከነሱ (ከአገሬው ተወላጆች) ሰምቻለሁ።" ይላል። በ13ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አረቡ የሥነ መልክዓ ምድር አጥኚ ኢብን ሰዒድ አል-ማግሪቢ እንዳለው ከሆነ የሀርላ አገር ከአቢሲንያ ግዛት በምስራቅ በኩል፣ ከዛንጅ ደግሞ በሰሜን በኩል የሚገኝ ነው። የዳግማዊ ሰዓድ አድ-ዲን የልጅ ልጆች የሆኑት የሀርላ ጎሳዎች በ16ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአቢሲንያ አዳል ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል። ኢብን ሰዒድም የሀርላ ግዛት ጥቁር አባይን ተሻግሮ በሰሜን ምስራቅ እስከ ባህሩ ዳርቻ ቅርብ ቦታ ድረስ እንደሆነ ይበልጥ አብራርቶቷል፤ ሀርላዎችም የወርቅ እና የብር ማዕድኖችን ቆፍረው እያወጡ በመሸጥ ይተዳደሩ ነበር። በኢትዮጵያ መዛግብት መሰረት በ14ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሀርላዎች በኢማም ሳሊህ እየተመሩ ከኢፋት ሱልጣኔት ጋር በመጣመር በአሁኗ ሰሜን ሶማልያ ከቀዳማዊ አፄ አምደ ጽዮን ሠራዊት ጋር ገጥመዋል። በ15ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘ-ኢትዮጵያ የጉንዳ ጉንዶውን አባ እስጢፋኖስ ብዙ ተከታዮች (ደቂቀ እስጢፋኖስን) ባርያ አድርጎ ለአዳል የሀርላ የባርያ ነጋዴዎች ሽጧቸዋል፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ይህንን ያደረገው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ዘንድ ኑፋቄ ተብሎ የተወገዘውን የአባ እስጢፋኖስን አስተምህሮ ስለተከተሉ እነርሱን ለመቅጣት ነበር በባርነት የሸጣቸው። በ16ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመርያ ላይ በሀረር የሀርላ ኢሚሮች እና በወላስማ ሥርወ መንግስት መካከል የሥልጣን ሽኩቻ ተፈጠረ። አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚም የወላስማውን ሱልጣን አቡ በከር ኢብን ሙሐመድን ገድሎ ሥልጣን ያዘ። በ16ተኛው ክፍለ ዘመን መሀል ላይ በነበረው በአዳሉ ጸሐፊ በአረብ ፋቂህም ጽሑፍ መሰረት የአዳል ሱልጣኔት በሀርላና በሶማሌ ጥምረት በመመራት አቢሲንያን ወረሩ። ሀርላዎችም መለሳይ የተባሉ የአዳል ቁንጮ ሠራዊት ክፍል ነበሩ። የኢትዮ አዳል ጦርነትም ለአዳሉ ሀርላ መሪ ለኢማም ማህፉዝ ሞት የተሰጠ ምላሽ ነበር። ኢማም ማህፉዝ የተገደለው በዳግማዊ ዳዊት(ልብነ ድንግል) የመጀመርያዎቹ የሥልጣን ዘመን ላይ አንድ ለአንድ በተደረገ ውግያ ላይ ነበር። አርበኛ መነኩሴ የነበሩት ገብረ እንድርያስም ከኢማም ማህፉዝ ጋር አንድ ለአንድ ገጥመው አሸነፈው ገደሉት። ኋላም ላይ ከሠርጸ ድንግል ጋር በተደረጉ ጦርነቶች ሀርላዎች በሱልጣን ሙሐመድ ኢብን ናስር ይመሩ ነበር። በ16ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መዝግያም ላይ የኦሮሞ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እና ሶማልያ ክፍሎች ጠልቀው በመግባት እየሰፉና እየወረሩ ታችኛው ጁባ ጋር ደረሱና በመጨረሻ የሀርላን አካባቢ ጠቀለሉ። እ.ኤ.አ በ1577ም ሀርላዎች የአዳልን ዋና ከተማ ወደ አውሳ ለምጌ አዘዋወሩ፤ ኋላም ላይ የአውሳ ኢማሜትን መሰረቱ፤ በ18ተኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የአውሳ ኢማሜት በአፋሩ ከሙዳይቶ ሥርወ መንግስት ተገለበጠ። እ.ኤ.አ በ1893 በብሪታንያ የሚመሩ ዘመቻዎች በሶማልያ ኑጋል ሸለቆ መጡ፤ የአካባቢው የድሁልባሃንቴ ጎሳም ከኦሮሞ ወረራ በፊት ሀርላዎች በአካባቢው ይኖሩ እንደነበር ተናግሯል። እ.ኤ.አ በ2017ም ጌጣጌጦችን ትሰራ የነበረች የሀርላ ከተማ በሥነ ቅርስ አጥኚዎች ተገኝታለች። በአካባቢው የተገኘው የመስጂዱ ሥነ ህንፃም ሀርላዎች በታንዛንያ እና ሶማልያ ከሚገኙ ኢስላማዊ ማዕከሎች ጋር ትስስር እንደነበራቸው ያሳያል። የሀርላ ነገድ መጥፋትም የ16ተኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮ አዳል ጦርነት፣ መደኽየት ወይም ወደ ሌላ ብሔረሰብ መጠቅለል ምክንያቶች እንደሆኑ ይነገራል። ጠንካራ ማስረጃም እንደሚያሳየው በኦሮሞዎች ስደት ወቅት ላይ የተቀሩት ሀርላዎች ወደ ሀረር ግንብ ገብተው ባህላቸውን ማትረፍ ቻሉ። ለድሬዳዋ በቅርበት የሚገኝ የሀርላ መንደር ላይ በሚነገረው ትርክት መሰረትም ሀርላዎች ከኦጋዴን የመጡ ገበሬዎች ነበሩ፤ የጠፉበትም ምክንያት በትዕቢታቸው፣ ረመዳንን አልፆምም በማለታቸው እና ቁርዓንን በሀርላ ቋንቋ ለመፃፍ በመሞከራቸው ነው፤ በዚህም አምላክ ረገማቸው ብለው ይናገራሉ የአካባቢው ሰዎች። በገዳቡርሲ ጎሳ ሰዎች እንደሚነገረውም ከሆነ ሀርላዎች ከፍተኛ ኩራት ስለነበራቸው ከፍተኛ ሐጢአቶች ሰርተዋል። ኤንሪኮ ሴሩሊ እና ሌሎች እንደሚሉትም ሀርላዎች ከሀረሪ አካባቢ የመነጩ ራሳቸውን የቻሉ ቡድኖች ናቸው። ነገር ግን አዳል ከወደቀች በኋላ በሶማሌዎችና በአፋሮች ተጠቀለሉ። ማጣቀሻ(Reference) https://en.wikipedia.org/wiki/Harla_people

Comment