MENU

Fun & Interesting

ቅድስት እንባ መሪና part-1 / Kidest Emba Merina - Ye Kidusan Tarik

Video Not Working? Fix It Now

ቅድስት እንባ መሪና በዘመነ ጻድቃን በምድረ ግብጽ የተወለደች:: ከአባቷ ጋር መንና ወደ ወንዶች ገዳም የገባች:: ወንድ መስላ የወንዶችን ቀኖና በምንኩስና የተቀበለች:: ያለ አበሳዋ ወንድ መስላቸው ዝሙት ሰርተሻል ተብላ ወደ በርሃ የተባረረች:: ያልወለደችውን ልጅ ያሳደገች:: ያለ ምግብና ውሃ ለ3 ዓመታት የተሰቃየች:: ብርድና ፀሐይ የተፈራረቀባትና: ስታርፍ ክብሯ የተገለጠላት ቡርክት እናት ናት:: ታሕሳስ 8 ልደቷ ነው፡፡ በረከቷ ይደርብን አምላከ ቅድስት እንባ መሪና ይቅር ይበለን፡፡ አሜን፡፡ ጻድቃን ጮሁ:: እግዚአብሔርም ሰማቸው:: ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው:: እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው:: መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል:: የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው:: እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል:: እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል:: መዝ. 33:17 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ከዲን ዮርዳኖስ ፅሁፍ የተወሰደ ይህን መንፈሳዊ ፊልም ተርጉመው ላቀረቡልን አጋፔ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት እግዚአብሔር ይስጥልን:: ክፍል አንድ (1) የማይሰራላችሁ ከሆነ ይህን ሊንከ ነክታችሁ ክፍል አንድን ማየት ትችላላችሁ (በድጋሜ አፐሎድ የተደረገ ነው) https://youtu.be/rMwUheNjWpk

Comment