የኦሮሞ የዘመቻ ታሪክ/The history of Oromo expansion/Babal'ina Oromoo
የኦሮሞ ዘመቻዎች በ16ተኛውና በ17ተኛው ክፍለ ዘመን በኦሮሞ ማኅበረሰብ የተካሄዱ የመስፋፋት ተግባራት ነበሩ። በ16ተኛው ክፍለ ዘመን ከተደረገው ታላቅ መስፋፋት በፊት የኦሮሞ ማኅበረሰብ ይኖር የነበረው በአሁኗ ደቡብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ኬንያ ብቻ ነበረ። በሂደትም በክፍለ ዘመናት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች በተለይም ደግሞ በሙስሊም አዳል ሱልጣኔት እና በክርስትያን አቢሲንያ ግዛት መካከል የነበሩት ጦርነቶች የሁለቱንም ማለትም የአዳልን እና የአቢሲንያን ወታደራዊ ኃይል ስላዳከመ ብዙ የኦሮሞ ጎሳዎች ዕድላቸውን በመጠቀም በአሁኗ ኢትዮጵያ ማዕከላዊና ምስራቃዊ ክፍሎች ወደሚገኙት አካባቢዎች ተስፋፉ።
በሉባ ቢፎሌ ዘመን የኦሮሞ ስደት የመጀመርያውን ትልቁን ስኬቱን አግኝቷል። ከዛ በፊት የነበሩት እንቅስቃሴዎች በጎረቤታቸው በሚገኙ ክፍለ ሀገራት ላይ የሚደረጉ ትናንሽ ማጥቃቶች ነበሩ፤ ነገር ግን በቢፎሌ አመራር ስር የአቢሲንያን ቁጥጥር ማዳከም የጀመሩ አዳዲስ ጥቃቶች መከናወን ጀመሩ። የደዋሮ ክፍለ ሀገር ሙሉ በሙሉ ወታደራዊ ዝርፍያ ተካሄደባት፤ ከደዋሮ በሰሜን የምትገኘው ፈጠገርም ለመጀመርያ ጊዜ ተጠቃች። ከዚህ በተጨማሪም ባህሬይ በገለጹት መሰረት የተዘረፉት አካባቢዎች ገባሪ ተደረጉ። አፄ ገላውዴዎስም በእነዚህ ጥቃቶች ምክንያት ወደ ደቡብ ዘመተ። በአፄ ገላውዴዎስ ዜና መዋዕል በተፃፈው መሰረት ንጉሰ ነገስቱ የኦሮሞ ወረራ ጥቃቶችን አሸነፈ፤ የማረካቸውን ደግሞ ለአመራሩ እንዲገዙ አደረጋቸው። ይህም ለጥቂት ጊዜ ያህል ጥቃቶች እንዳይደረጉ አግዶ ነበረ። የመጀመርያዎቹ ጥቃቶች ታላላቅ ስለነበሩ፤ ለአቢሲንያው ሥርወ መንግስት አውዳሚ ነበሩ። ገላውዴዎስ አጸፋዎችን ቢመልስም አደጋ ውስጥ ነበረ፤ በ1550ዎቹ መጀመርያም ተፈናቃዮቹን ከዝዋይ ሐይቅ በሰሜን በሚገኘው በወጅ ከተማ ማስፈር ግድ ሆነበት።
የኦሮሞ መስፋፋቶች ግን በአቢሲንያ የተገደቡ ብቻ አልነበሩም፤ ወደ አዳልም የሚሄዱ ነበሩ እንጂ። ለምሳሌ ያህል የኦሮሞ ሠራዊት የሀረር አሚር የነበረው የኑር ኢብን ሙጃሂድ ሠራዊትን በሀዛሎ ጦርነት ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ አሸንፎታል።
በ1710 አካባቢ የሜጫ ኦሮሞ በጊቤ አካባቢ ወደምትገኘው ሺሻፎትቺ በተባለ ንጉስ ወደምትመራው ወደ ጎንጋዋ ግዛት ኢናርያ ደረሰ። የኢናርያ ንጉስም ግዛቶችን በመጠቅለል ጉጉት የተጠመዱትን የሜጫ ኦሮሞዎችን ወደ አመራሩ በማስገባት ነገሩን ለመወጣት ሞከረ። ነገር ግን ይህ ተግባሩ ለጥፋቱ መንስኤ ሆነው። በሥልጣን ቦታዎችም ለኦሮሞ በማድላቱ ምክንያት ንጉሱ ሺሻፎትቺ የራሱ ህዝብ ጠላው። በሥልጣን ቦታ የሚገኙት ኦሮሞዎችም በህዝቡ ዘንድ ያለውን ንዴት ለራሳቸው ጥቅም በማዋል ንጉሱን ከሥልጣኑ አውርደው ግዛቱን በእጃቸው ሥር ከተቱ።
በተጨማሪም በ18ተኛው ክፍለ ዘመን የሜጫ ኦሮሞዎች የጎጀብ ወንዝን በመሻገር በከፋ ግዛት ላይ ወረራ መሩ። በዛም አዳጋች የሆኑ ተፈጥሮአዊ ኬላዎች ገጠሙዋቸው፤ ወደ ከፋም እንዳይገቡ ከለከላቸው። በተራራማው ጫካም የከፋ ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከል ፈጣን የሆነ የፈረሰኛ ጥቃት በሜጫ ኦሮሞዎች ላይ አደረጉባቸው፤ ከዛም ጫካ ውስጥ ከፈረሰኞቹ አምልጦ መሸሽ የማይቻል ጉዳይ ነበረ፤ ዘመቻቸውም በከፊቾ ህዝብ ታገደ። ነገር ግን የሜጫ ኦሮሞዎች ከጎጀብ ወንዝ በሰሜን የሚገኙትን አካባቢዎች የጅማ ከተማን ጨምሮ ተቆጣጠሩ።
የኦሮሞ መስፋፋት በአሁኗ አፍሪካ ቀንድ ትልቅ ተፅዕኖ አለው። ኦሮሞም በአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆነ። በዚህም የክርስትያን አቢሲንያን በማዳከም የአቢሲንያን የሥልጣን ቦታዎችን በመያዝ ወደ ዘመነ መሳፍንት ከተታት። በዛም በአብዛኛዎቹ የአቢሲንያ ክፍለ ሀገራት ላይ ቀጥተኛ ሥልጣን በማግኘት ንጉሰ ነገስታቱን አቀያየሩ፤ በዘመኑም ንጉሰ ነገስታቱ እንደ አሻንጉሊት የሚቀመጡ ነበሩ።
ማጣቀሻ(Reference)
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Oromo_expansion