የሀገራችን የኢትዮጵያ
ሊቁ ገበሬ በዕምነቱ ፅኑ
በስራው ታታሪ ነው
ስለሀገሩ ታሪክ ጠንቅቆ የሚያውቅ
በሀገር ፍቅርልቡም የተሞላ
ድንበሩንም የሚያስጠብቅ
ጀግናም ነው በእውነት
ከገበሬው ብዙ የምንማረው
ነገር አለና
እውቀቱንም እንሽምት
ያረስው በቅሎ
ጎተራውን አምላክ
በእህል ይሙላለት
ሊቁን ገበሬን ያለምልምልን
ሥራውን በምስጋና ጀምሮ
ገበታው ባርኮ የሚመገበውን
በልቶ ሲጨርስ የሚ መርቀውን
ደጉን ገበሬ ይጠብቅልን
ፈጣሪ!