Kesis Hailemelekot Girma Wondimu
ይህ ቻናል የቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ ትክክለኛው ቻናል ሲሆን እዚህ ቻናል ውስጥ በመሠረታዊ ምድብ በሦስት የተከፈሉ አባላት ይኖራሉ፡፡ አንደኞቹ፤ ከዚህ ቀደም ጭራሽ የአምልኮተ እግዚአብሔርን ትምህርቶች አግኝተው የማያውቁ፣ መንፈስ ማለት ከውስጥ ሳይሆን ከውጪ ያለ ጠላት እንደሆነ በተለምዶ የሚያስቡ፣ በቤት ጸሎት ቦታ አዘጋጅተው መስገድ መንበርከክ ያልጀመሩ ናቸው፡፡ ሁለተኛዎቹ፤ አስቀድሞ የመልአከ መንክራት መምህር ግርማን ትምህርት ተከታትለው ጥሩ መረዳትን የያዙ፣ ስለ ክፉ መንፈሶች ዘርፈ ብዙ የጥፋት ዘዴና ውጊያ የተገነዘቡ፣ የአምልኮትን ልምምድና ወደ ጽድቅ መንገድ የሚመራውን ትግል የጀመሩ፣ ተጨማሪ መረጃዎችንና ልምዶችን ከዚህ ቻናል ለማግኘት የተቀላቀሉ አሉ፡፡ ሦስተኛዎቹ፤ በመንፈሳዊው ዓለም ያለውን የብርሃንና የጨለማ ኃይል ጦርነት አስርጸው በእጅጉ ያወቁ፣ ለረጅም ዓመታት በመስገድ በመጸለይና መናፍስትን በመፋለም ብዙ ልምድ ያካበቱ፣ እያንዳንዷን ሰኮንድና የሕይወት ክስተትን በንቃት የሚያዩ፣ በዓይን ከሚታዩ ነገራት ጀርባ ያለውን በሥጋ የማይታይ የዲያቢሎስ ፈተና የሚያዩ፣ ፍጹም ከዘልማዳዊ አስተሳሰብና ሕይወት የተላቀቁ እና ክርስትናን እያወሩ ሳይሆን እየኖሩ ያሉ ደግሞ ሰዎች አሉ፡፡ እዚህ ቻናል ውስጥ ታዲያ የሚተላለፈውን አንድ ትምህርት፤ መንፈስ ቅዱስ ሦስት ቦታ እየበተነ ለሁሉም በሰዓቱ የተፈቀደለትን ያህል እንዲገነዘብ የእግዚአብሔር ኃይል ድንቅ ሥራውን ያከናውናል፡፡
Subscribe, Share, Like, Comment እያደረጋችሁ ላልሰሙት አሰሙ ላልነቁ አንቁ! መንፈሳዊነት ይብለጥ! የማዳመጥ ጊዜ ላይ ነን!!!