ጸጋ መልቲ ሚዲያ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ በምትገኘው የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሕብረት ቤተክርስቲያን የተዘጋጀ የዩቲዩብ ቻናል ነው። ከቤተክርስቲያኗ ራዕይና ተልዕኮ በመነሳትም ወንጌልንና ክርስቶስ ተኮር የሆኑ የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ወደትውልዱ ለማድረስ ታቅዶ ተመስርቶዋል። ስለዚህም ጸጋ በሳምንት አንድ ቀን በተለያየ መልክና ይዘት ስብከቶችን፣ ትምህርቶችን፣ ዝማሬዎችን፣ ቃለ መጠይቆችንና እንዲሁም ስነ ጽሁፎችን እያዘጋጀ ለእናንተ ያቀርባል። እባክዎ ይህን ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግና በፀሎት በመደገፍ የዚህ ራዕይና አገልግሎት አጋርና ተሳታፊ እንዲሆኑ በማክበር ጋብዘነዎታል።