Kidist Arsema Maryland || ቅድስት አርሴማ ሜሪላንድ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ግዛት በካሎር ካውንቲ በዌስት ሚንስተር ( ማንቺስተር ) ጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እና የምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳም ተብሎ ሲጠራ ሥፍራውንም የጀመረ ያዘጋጀና የፈጸመው እግዚአብሔር ነው።
“ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሐነጻ ወልድ ለዛቲ ቤት ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ”
ይህችን ቤት አብ አስቀድሞ መሠረታት፣ ወልድ ገነባት፣ መንፈስ ቅዱስ ፈጸማት ::