Research(ጥናትና ምርምር)1. የጥናትና ምርምር የመረጃ ምንጮች(Source of data)2. ናሙና አመራረጥ (Sampling)
ለጥናታዊ ምርምር የሚያስፈልግ መረጃ ከሁለት ዋና ዋና ምንጮች ሊሰበሰብ ይችላል።
እነርሱም:-
1. ርቱዕ ምንጭ / Primary source/ እና
2.ኢርቱዕ ምንጭ /Secondary source/
በመባል ይታወቃሉ፡፡
ለጥናታዊ ምርምር የሚያስፈልጉ መረጃዎች በተለያዩ ዘዴዎች አማካኝነት ይሰበሰባሉ፡፡
ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ/ የጽሑፍ መጠይቅ (Questionnaire)
ለ/ የቃል መጠይቅ (Oral Interview)
ሐ/ የስለክ መጠይቅ (Telephone interview)
ሐ/ የመስክ ምልከታ (Observation)
መ/ የተመረጠ ቡድን ውይይት (Focus Group Discussion)
እነዚህ ዘዴዎች የራሳቸው የሆነ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ስላላቸው የተመራማሪውን ጥንቃቄና ትኩረት ይሻሉ፡፡
ናሙና አመራረጥ (Sampling)
የጥናቱ አካል የሆነውን ስብስብ በሙሉ /1ዐዐ%/ መውሰድ በማይችልበት ሁኔታ ናሙና እንጠቀማልን፡፡ ናሙና ከአጠቃላይ ስብስብ (Population) ውስጥ ስብስቡን ለመወከል በሚመች መልክ ለጥናታዊ ምርምር የሚወሰድ የመረጃ ማግኛ ክፍል ነው፡፡ አብዘኛውን ጊዜ ናሙና የሚወሰደው በአጠቃላይ ስብስቡ ውስጥ ያሉ ጥናቱ የሚነካቸው ሰዎች ወይም ሁኔታዎች ብዛትና ስፋት ሲኖራቸውና ከጊዜ፣ ከገንዘብና ከሰው ኃይል አንፃር አንድ ላይ ለመጠናት የማይችሉ ሲሆን ነው፡፡
ናሙና በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ሊከፈል ይችላል፡፡ እነርሱም፡-
1. ግምት ሰጭ ናሙና (Probability sampling)
2. ግምት የማይሰጥ ናሙና (non-probability sampling)