ርጢን ከሙጫ ተቀምሞ የሚዘጋጅ ልዩ ፈዋሽ ዕጣን ነው፡፡ ዕጣን ከ ብሉይ ኪዳን ጀመሮ መሥዋዕት ማሳረጊያነቱ በላይ ፈዋሽ መዓዛ ያለው በመሆኑ የራሱ ልዩ የነፍስ መዓዛ ያለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ በጸሎተ ቅዳሴያችንም ላይ ''ዕፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ... ዕጣን ይእቲ ማርያም ፣ዕጣን ውእቱ እስመ ዘውስተ ከርሣ ዘይትሜዐዝ እምኵሉ ዕጣን ዘወለደቶ መጽእ ወአዳኃነነ'' እያልን የምንጠራው አማናዊው ልዩ መዓዛ ያለው ፈዋሽ መድኃኒት ነው፡፡
የዚህ ምዕላፍ ይዘትም ይህንኑ የነፍሳችንን መድኃኒትየሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነትና የምንድንበትን መንገድ በተቀመመ መንገድ በሂደት አብስሎ በዝርዝር የሚያስረዳ ስለሆነ ''ርጢን'' ተብሏል፡፡ በዚህ ምዕላፍ ላይ ተከታታይ ትምህርቶች፣ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ህይወተ ወራዙትን፣ ምስጢሬን ላካፍላችሁ፣ከመጽሐፍት አምድንና ሌሎችን ዝርዝሮች የያዘ ሲሆን በእነዚህ ምዕላፎች የሚዳሰሱት፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ፣አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች፣ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ፣ወቅታዊ መረጃዎችና ስብከቶችን የሚያቀርብበት ነው፡፡