ባለታርካችን ከኢትዮጲያ ወደ ታንዛኒያ ተሽጣለች::
ጅማ ውስጥ ማንም የማይደፍራት ተደባዳቢ ነበረች::
አባቷን አታውቀውም::
እናቷ ስትሞት ታላቋ ትምህርት አቁማ ካፌ እየሰራች እሷን ማስተማር ጀመረች::
እያደገች ስትመጣ ግን ፈነዳች::
ከጏደኞቿ ጋር መቃም መጠጣት ማጨስ ጀመረች::
በወቅቱ ጅማ ውስጥ ዝነኛ የቡድን ጥል መሪ ሆነች::
የታክሲ ሹፌር አግብታም ወለደች::ትዳሩንም አፈረሰች::
ከቤተሰቦቿ ጋር ተጣልታ ወደ አዲስ አበባ
መጣች::በምትሰራበት መስርያ ቤት የተተዋወቀቻት እናት ከልጇ ጋር አሳዛኝ ድርጊትን ፈፀሙባት::በትዳር ሰበብ ወደ ታንዛኒያ ሸጧት::ህይወታቸውን ተለወጡባት::
በህይቷ ብዙ ውጣውረድ አልፋ ዛሬ በማንያዘዋል እሸቱ ግቢ ታሪኳን ትተነፍሳለች::