የመጨረሻ እንባዬን አነባሁ ተንሰቅስቄ አለቀስኩኝ ድንገት ከመሬት ሊያነሳኝ ፈርጠም ያለ እጅ ክንዴ ላይ አረፈቀና ብዬ አየሁት አረመኔው ሰው ነበር...
እግሬ ግን ብዙ ሊያራምደኝ አልቻለም፡፡ ክፉኛ የተመታው ከጉልበቴ በታች ያለው አካሌ እርምጃዬ በጀመረ ቁጥር በእጥፍ ስቃዬን ይበረታል፡፡ ተማርኮ ከመሞት እየሸሹ መሞት ለኔ ክብር አለው፡፡ "ቆሜማ አልሞትም አዎ አልሞትም" አልኩኝ ለራሴ፡፡ ትንሽ እንደተራመድኩ ከአንዱ ክፍል ውስጥ በሰመመን የሚያቃስት የሲቃ ድምፅ ደረሰኝ፡፡ እንደኛው እድል ዞራበት ወደ ሞቱ የገሰገሰ የገዳይ ግዳይ ሊሆን የተዘጋጀ የመስዋዕት በግ ይሆን እንደሁ ብዬ ወደ ክፍሉ ገባሁ፡፡